am_tn/hos/10/10.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

እጥፍ ኃጢአት/በደል

ይህ የሚያመለክተው የእስራኤልን የኃጢአት ብዛት ነው፡፡ ኤፍሬም እንደ ተገራች መውቃት እንደምትወድ ጊደር ነው ጊደር ማበራየት ትወዳለች ምክንያቱም ቀንበር ሳይጫንባቸው በነጻነት በዙሪያ መዞር ይችላሉ፡፡ ያህዌ የእስራኤል ህዝብ ነጻ ሆኖ ያሻውን ደስተኛ ህይወት መኖር ይችላል እያለ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በምቹ ጫንቃዋ ላይ ቀንበር እጭናለሁ፣ በኤፍሬም ላይ ቀንበር አስቀምጣለሁ

እዚህ ስፍራ "ቀንበር" የሚያመለክተው መከራን እና ባርነትን ነው፡፡ ያህዌ ለእስራኤል ህዝብ ደግ ነበር፣ ህዝቡ ግን ለእርሱ ታማኝ አልበረም፡፡ ስለዚህም እርሱ ይቀጣቸዋል ደግሞም ለባርነት አሳልፎ ይሰጣቸዋል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይሁዳ ያርሳል፣ ያዕቆብ መሬቱን ያለሰልሳል

እዚህ ስፍራ "ይሁዳ" የሚያመለክተው የደቡቡን መንግሥት ህዝብ ነው፤ "ያዕቆብ" ደግሞ የሰሜኑን መንግሥት ህዝብ ያመለክታል፡፡ ይህ ማለት እግዚአብሔር በሁለቱም መንግሥታት ላይ አስጫቂ ጊዜን ያመጣል ማለት ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

መከስከሻ

መሬትን ለማለስለስ እና ከታረሰ በኋላ ዘርን አፈር ለማልበስ የሚያገለግል መሳሪያ