am_tn/hos/10/09.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

በጊብዓ ዘመን

ይህ ምናልባት በመሳፍንት ምዕራፍ 19 እስከ ምዕራፍ 21 በሚገኘው ታሪክ ውስጥ በብንያም ነገድ ከተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት ጋር የሚነጻር ነው፡፡ ይህንን በሆሴዕ 9፡9 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡

በዚያ እናንተ ታስታውሳላችሁ

ይህ ክፍል ምናልባት በጊዜው የነበሩ ሰዎች አባቶቻቸው በጊብዓ ያደርጉት የበረውን በተመሳሳይ መንገድ ማድረግ ቀጥለው ሊሆን ይችላል፡፡ "እናንተም ልክ እነርሱ ያደርጉት እንደነበረው ታስባላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጦርነት በጊብዓ የኃጢአተኞችን ልጆች አልጨረሰምን?

ያህዌ ጥያቄውን የተጠቀመበት በጊብዓ ኃጢአተኞች በራሳቸው በእርግጥ ጦርነቱን መወጣት እንዳለባቸው በአጽንኦት ለመናገር ነው፡፡ ደግሞም ይህ ሲገለጽ ሰዎቹ ጦርነትን መወጣት ያለባቸው ጠላቶቻቸው ሲመጡባቸው ጦርነት ሰው ሆኖ እንሚይዛቸው ተደርጎ በማቅረብ ነው፡፡ "ጦርነት በእርግጥ በጊብዓ ኃጢአት ባደረጉ ላይ ይመጣባቸዋል" ወይም "ጠላቶች በእርግጥ በጊብዓ ኃጢአት የሰሩትን ያጠፋቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

የኃጢአተኞች ልጆች

እዚህ ስፍራ "የአባቶቻቸው ልጆች" የሚለው ፈሊጥ ነው፤ ትርጉሙ "የአባቶቻቸው ባህሪ ያላቸው" ማለት ነው፡፡ "ኃጢአት ያደረጉ" ወይም "ክፉ አድራጊዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)