am_tn/hos/10/05.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሆሴዕ ስለ እስራኤል እየተናገረ ነው፡፡

ቤትአዌን

ይህ ከተማ በእስራኤል ሰሜናዊ ግዛት እና በደቡባዊ ግዛት በቢንያም ነገድ ድንበር መሃል የሚገኝ ነበር፡፡ ይህንን በሆሴዕ 4፡15 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ አሦር በምርኮ ይወሰዳሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አሦራውያን እነርሱን በምርኮ ይወስዷቸዋል" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ኤፍሬም ይዋረዳል፣ እስራኤልም በጣኦቷ ታፍራለች

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ደግሞም የእስራኤል ህዝብ በጣም ያፍራል፤ ምክንያቱም ጣኦታትን አምልኳልና " በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ጣኦቷ

ብዙ ቅጂዎች በዚህ ክፍል የሚገኘውን የዕብራይስጡን ቃል "ምክር፣" "እቅድ፣" ወይም "አስተሳሰብ" ብለው ተርጉመዋል