am_tn/hos/10/03.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሆሴዕ ስለ እስራኤል እየተናገረ ነው፡፡

እናም ንጉሡ - ለእኛ ምን ማድረግ ይችላል?

ህዝቡ ንጉሦቻቸው ሊረዷቸው እንዳልቻሉ ይናገራሉ፡፡ "ምንም እንኳን አሁን ንጉሥ ቢኖረንም፣ እኛን ሊረዳን አልቻለም " በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ባዶ/የማይጠቅሙ ቃላትን ይናገራሉ

እዚህ ስፍራ "ባዶ /የማይጠቅሙ ቃላት" የሚለው የሚያመለክተው ሃሰትን ነው፡፡ "ሃሰት ይናገራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህ በእርሻ ዳርቻ እንደሚበቅል መርዛማ አረም ፍርድ ፈጥኖ ይበቅላል

እነዚያ ሰዎች በህጎቻቸው እና በህጋዊ ውሳኔዎቻቸው ፍርድ ብለው የሚጠሩት የተገለጸው ፈጥኖ እንደሚያደነቁል/እንደሚበቅል ተክል ነው፡፡ "ስለዚህ ውሳኔዎቻቸው ፍትሃዊ አይደሉም፣ ይልቁንም ጎጂዎች ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሻ ዳርቻ እንደሚበቅል መርዛማ አረም

የእነርሱ ሃሰት እና ፍትህ አልባነት በህዝባቸው መሃል ተስፋፍቶ እንደ መርዛማ ተክሎች ሁሉንም ሰው ጎዳው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)