am_tn/hos/10/01.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሆሴዕ ስለ እስራኤል እየተናገረ ነው፡፡

እስራኤል ብዙ የሚያፈራ የተንዠረገገ የወይን ተክል ነው

እስራኤል የተገለጸችው በጣም ፍሬያማ እንደሆነ የወይን ተክል ነው፡፡ ህዝቡ ለጊዜው በለጽጎና ጠንክሮ ነበር፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የተንዠረገገ የወይን ተክል

ይህ ወይን ከተለመደው ይበልጥ ያፈራል ፍሬው በመመረለት መጠን… ምድሩ ብዙ ሲያፈራ እነዚህ ሁለቱም አገላለጾች፤ ህዝቡ ሲበለጽግ፣ እየጠነከረ እና ሃብት እያገኘ ሲመጣ የሚል ተመሳሳይ ትርጉም ይሰጣሉ፡፡

ልባቸው በማታለል የተሞላ ነው

"ልባቸው" የሚለው የሚገለጸው መላው ማንነታቸውን፣ በስሜታቸው እና ፍላጎታቸው ላይ ትኩረት በማድረግ ነው፡፡ "እነርሱ አታላዮች ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲኪ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

አሁን ኃጢአታቸውን መሸከም አለባቸው

እዚህ ስፍራ "ኃጢአት" የሚለው ከዚህ ጋር ለተያያዘ የሚደርስ ቅታትን የሚያመለክት ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ይህ ቅጣት የተገለጸው ለመሸከም ከባድ እንደሆነ ክብደት ነው፡፡ "አሁን ያህዌ በኃጢአታቸው ምክንያት የሚቀጣቸው ጊዜ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)