am_tn/hos/09/13.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ነቢዩ ሆሴዕ እየተናገረ ነው

ልክ እንደ ጢሮስ፣ ኤፍሬምን በለምለም መስክ ተተክሎ አየሁት

ይህ ህዝቡ በለምለም መስክ እንደ ተተከለ ዛፍ በመልካም ስፍራ እንደሆነ ይናገራል፡፡ "የእስራኤል ህዝብ በአንድ ወቅት እንደ ጢሮስ ከተማ፣ ደግሞም በለመለመ ምስክ እንደ ተተከለ ዛፍ ውብ እና አስደሳች ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ኤፍሬም … ጢሮስ

እዚህ ስፍራ "ኤፍሬም" የሚለው የሚወክለው መላውን የእስራኤል ህዝብ ነው፡፡ እነዚህ ስፍራዎች በውስጣቸው የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታሉ፡፡ (ስኔክቲኪ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

ነገር ግን ኤፍሬም ልጆቹን አሳልፎ ይሰጣል

"ልጆች" የሚለው ቃል የአገሪቱን ሰዎች ያመለክታል፡፡ "ነገር ግን የእስራኤል ሰዎች ልጆቻቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚውን ይመልከቱ)

ያህዌ ሆይ አድርግባቸው፣ - ምን ታደርግባቸዋለህ? እባክህ አድርግባቸው

ሆሴዕ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው ያህዌ ለእስራኤል ህዝብ የሚገባቸውን እንዲያደርግባቸው በጉልህ ማሳየት ስለፈለገ ነው፡፡ " ያህዌ ሆይ፣ እኔ የምጠይቀው ይህንን ነው፤ እንድታደርግባቸው፣ እባክህን ስጣቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ)

ጽንስ የማይሸከም ማህጸን

"የማይሸከም" ማህጸን ማለት ጽንሱ እንዲጨነግፍ እና የተረገዘው እንዲሞት ማለት ነው፡፡ ሆሴዕ የአገሪቱ ሴቶች ሁሉ እንደዚያ እንዲሆኑ እየጠየቀ ነው፡፡