am_tn/hos/09/10.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

እኔ እስራኤልን ሳገኛት

ይህ የሚያመለክተው ያህዌ ከእስራኤል ህዝብ ጋር እነርሱን የራሱ ልዩ ህዝብ አድርጎ ለይቶ በመጀመሪያ ግንኙነት መጀመሩን ነው፡፡

ይህ በበረሃ ወይን፤ በበለስ ዛፍ ላይ እንደ የወቅቱን የበኩራት ፍሬ እንደማግኘት ነበር፡፡

እነዚህ ሁለቱም ሃሳቦች የሚያጎሉት አንድን ሰው ደስ የሚያሰኙትን ሁኔታዎች ነው፡፡ ይህ ማለት ከእስራኤል ህዝብ ጋር ግንኙነት ሲጀመር ያህዌ እጅግ ደስተኛ ነበር፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

በዓል ፌጎር

ይህ በሞዓብ ምድር የሚገኝ የበዓል ሃሰተኛ አማልዕክት ይመለኩበት የነበረበት ተራራ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)