am_tn/hos/09/08.md

2.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ነቢዩ ሆሴዕ እየተናገረ ነው

ነቢዩ በኤፍሬም ላይ ለአምላኬ ዘበኛ ነው

"ዘበኛ" ከከተማ ውጭ ሆኖ አደጋ መምጣት አለመምጣቱን ይጠብቃል፡፡ ነቢዩ ህዝቡ ኃጢአት ሲሰራ እና አምላኩ ህዝቡን ሊቀጣ ባለበት ጊዜ ለከተማይቱ እንደ ዘበኛ ሆኖ ያስጠነቅቃል፡፡ "ነቢዩ በኤፍሬም ላይ ለእግዚአብሔር እንደ ዘበኛ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ነቢዩ በኤፍሬም ላይ ለአምላኬ ዘበኛ ነው

አንዳንድ ትረጉሞች ይህንን ክፍል "ነቢዩ ከአምላኬ ጋር በኤፍሬም ላይ ዘበኛ ነው" ብለው ይተረጉሙታል፡፡

ነቢዩ ነው

ይህ የሚያመለክተው በአጠቃላይ እግዚአብሔር ለሾማቸው ነቢያት ሁሉ ነው፡፡ "ነቢያት ናቸው" ወይም "እውነተኛ ነቢያት ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የጋር/የወል ስማዊ ሀረግ የሚለውን ይመልከቱ)

ኤፍሬም

እዚህ ስፍራ "ኤፍሬም" የሚለው የሚወክለው መላውን የእስራኤል ህዝብ ነው፡፡ (ስኔክቲኪ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የወፍ ወጥመድ በመንገዱ ሁሉ ነው

የ "ወፍ ወጥመድ" ወፍን ለመያዝ የሚያገለግል ማጥመጃ ነው፡፡ ይህ ማለት የእስራኤል ህዝብ የእግዚአብሔርን ነቢይ ለማስቆም የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ "ህዝቡ በሚሄድበት ሁሉ ለእርሱ ወጥመድን ያስቀምጣሉ" ወይም "ህዝቡ እረሱን ለመጉዳት የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በጊብዓ ዘመን እንደነበረው ራሳቸውን እጅግ በኃጢአት በክለዋል

"የእስራኤል ህዝብ ኃጢአት በማድረግ ከዘመናት አስቀድሞ በጊብዓ ዘመን ያደርጉት እንደነበረው እጅግ ረክሰዋል" ይህ ምናልባት በመሳፍንት ምዕራፍ 19 እስከ ምዕራፍ 21 በሚገኘው ታሪክ ውስጥ በብንያም ነገድ ከተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት ጋር የሚነጻር ነው፡፡