am_tn/hos/09/07.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ነቢዩ ሆሴዕ እየተናገረ ነው

የቅጣት ቀናት እየመጡ ነው፣ የፍርድ ቀናትም እየመጡ ነው

ሆሴዕ እነዚህን ሁለት ተመሳሳይ ነገሮች የሚናገረው ያህዌ የእስራኤልን ህዝብ ለክፉ ተግባሮቻቸው በቶሎ እንደሚቀጣ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን መልከቱ)

ነቢዩ ሞኝ ነው፣ መንፈሳዊ ነኝ ሚለውም ሰው እንደ እብድ ነው

እነዚህ ሀረጋት በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ አማራጭ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሰዎች ነቢዩን እንደ እብድ ሰው ይቆጥሩታል ወይም 2) ነቢያት ህዝቡ ከሚሰራው ኃጢአት የተነሳ እንደ አብድ ሆንነዋል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ነቢዩ ሞኝ ነው፣ መንፈሳዊ ነኝ ሚለውም ሰው እንደ እብድ ነው

እዚህ ስፍራ "ነቢይ" እና "መንፈሳዊ ሰው" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ከእግዚአብሔር መልዕክት ተቀብያለሁ የሚልን አንድ ሰው ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ሃሰተኛ ነቢያት መሆናቸው ተመላክቷል፤ እነርሱ ራሳቸው ብቻ ከእግዚአብሔር መልዕክት ተቀብያለሁ ሲሉ ያስባሉ፡፡ (ጥንድ ትረጉም እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

በታላቅ ኃጢአታችሁ እና በታላቅ ጠላትነታችሁ ምክንያት

"ታላቅ ኃጢአት" እና "ታላቅ ጠላትነት" የሚሉት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉምን ይጋራሉ፡፡ የህዝቡ ኃጢአተኛነት ራሱን የሚገልጸው በያህዌ እና በነቢያቱ ላይ ባላቸው ጠላትነት ነው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)