am_tn/hos/09/05.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ነቢዩ ሆሴዕ እየተናገረ ነው

በያህዌ በዓል ዕለት፣ በተወሰነው ክብረ በዓል ምን ታደርጋላችሁ?

ሆሴዕ ይህንን ጥያቄ ያነሳው ህዝቡ ክብረ በዓሉን ስለረሳ፣ ጠላቶቻቸው ስላሸንፏቸው እና በምርኮ ስለወስዷቸው፤ በዓሉን ማክበር አለመቻላቸውን ማጉላት ስለፈለገ ነው፡፡ "ያህዌ ለእናንተ የወሰነውን ክብረ በዓል ማክበር አትችሉም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የተወሰነው የክብረ በዓሉ ቀን… ለያህዌ ክብረ በዓል ቀን

ሁለቱም አገላለጾች አንድ ትርጉም አላቸው (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቢያመልጡ እንኳን

እዚህ ስፍራ "እነርሱ" የሚለው አሁንም የሚገልጸው የእስራኤልን ህዝብ ነው፡፡ ይህንን በሁለተኛ መደብ በመግለጽ መቀጠል ይችላሉ፡፡ "አንተ ብታመልጥ" በሚል፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ግብፅ ይሰበስባቸዋል፣ ደግሞም ሜምፎስ ይቀብራቸዋል

ግብፅ እና ሜምፎስ በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ "የግብፅ ሰራዊት ይማርካችኋል፡፡ እናንተ በዚያ ትሞታላችሁ፣ በሜምፎስ ከተማ የሚኖሩ ሰዎች ይቀብሯችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የብር ሃብታቸውን እሾሃማ ቁጥቋጦ ይወርሰዋል

ቁጥቋጦ እስራኤላውያን ብራቸውን ባከማቹበት ስፍራ ይበቅላል የተባለው ቁጥቋጦ እንደ ሰብአዊ ጠላት ሆኖ ውድ ሃብታቸውን ለራሳቸው እንደወሰዱ የተገለጸበት ነው፡፡ "እሾሃማ ቁጥቋጦ የብር ሃብቶቻቸውን ባከማቹበት ስፍራ ይበቅላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እሾሃማ ቁጥቋጦ ይወርሳቸዋል፣ እሾህ ድንኳኖቻቸውን ይሞላዋል

እዚህ ስፍራ "እሾሃማ ቁጥቋጦ" እና "እሾህ" የሚለው ተመሳሳይ ነገርን ይገልጻል፡፡ እሾሃማ ቁጥቋጦ እና እሾህ ማደጉ የሚወክለው ሰው የማይኖርበትን ምድር እና በረሃማነትን ነው፡፡ (ጥንድ ትረጉም እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

የእነርሱ ድንኳኖች

እዚህ ስፍራ "ድንኳኖች" የሚለው የሚወክለው የእስራኤላውያንን ቤቶች ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)