am_tn/hos/09/03.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ነቢዩ ሆሴዕ እየተናገረ ነው

የያህዌ ምድር

ይህ አገላለጽ የሚያመለክተው ያህዌ የእስራኤልን ምድር እንደ እስራኤላውያን ንብረት ሳይሆን እንደ ራሱ ንብረት ማየት መቀጠሉን ነው፡፡

ንጹህ ያልሆነ ምግብ

ይህ እስራኤላውያን በያህዌ ዘንድ ተቀባይነት ያሳጣናል በማለት ሊመገቡት የማይፈቅዱት ምግብ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መስዋዕታቸው እንደ ለቀስተኞች ምግብ ይሆንባቸዋል

እዚህ ስፍራ "የቀስተኞች ምግብ" የሚለው የሚያመለክተው ሰዎች በለቅሶ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ የሚመገቡትን ነው፣ ምክንያቱም በልቅሶ ላይ ሲሆኑ ስለሚረክሱ እና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ስለሚያጡ ነው፡፡ ይህ ማለት ያህዌ የህዝቡን መስዋዕት እንደ ረከሰ ይቆጥረዋል ደግሞም እነርሱንም አይቀበላቸውም፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የእነርሱ ምግብ ለእነርሱ ብቻ ይሁናቸዋል፤ ወደ ያህዌ ቤት አይመጣም

የእስራኤል ህዝብ የሚመገቡት ምግብ ይኖራቸዋል፣ ነገር ግን ያህዌ ያንን በመስዋዕትነት አይቀበለውም

ወደ ያህዌ ቤት አይመጣም

ንጹህ ያልሆነው ምግብ ወደ ስፍራዎች በራሱ መሄድ እንደሚችል ተደርጎ ተነግሯል፡፡ እወነታው ግን በእርግጥ፣ ሰዎች ይዘውት ሊሄዱ ያስፈልጋል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)