am_tn/hos/09/01.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ነቢዩ ሆሴዕ እየተናገረ ነው

ነገር ግን የእህል አውድማ እና የወይን መጭመቂያው እነርሱ አይመግባቸውም

ይህ የሚገልጸው የእህል አውድማ እና የወይን መጭመቂያው ራሳቸው ሌላውን የሚመግቡ ሰዎች እንደሆኑ ተድርጎ ነው፡፡ ይህ ማለት መከሩ የህዝቡን ፍላጎት ለማሟላት የሚበቃ የፍሬ አይሰጥም፣ የወይን መከሩም በቂ የወይን ጠጅ አይሰጥም ማለት ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

የእህል አውድማ

ይህ እህል ለመውቃት የሚውል ሰፊ ስፈራ ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ለማህበራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ማክበሪያ የሚያገለግል ስፍራም ነው፡፡ የቤተ ጣኦት ዘማዊያት ለጣኦት የሚደረገውን የመከር በዓል ለማክበር ወንዶቹን ለመርዳት ይመጣሉ፡፡

አዲሱ ወይን አይበቃቸውም

ወይን ጠጅ ለማዘጋጀት በቂ የወይን ጭማቂ አይኖርም