am_tn/hos/08/08.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

እስራኤል ተዋጠች

"ተዋጠች" ማለት መሸነፍ እና በምርኮ መወሰድ ማለት ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የእስራኤል ጠላቶች እስራኤላዊያንን ወደ ሌላ ምድር ወሰዷቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

እንደ ዱር አህያ ብቻቸውን

ሰዎች ብዙውን ጊዜ አህያን እንደ ደደብ/ግትር ይቆጥራሉ፡፡ ይህ ማለት የእስራኤል ህዝብ ያህዌን መስማትን ይቃወማል ነገር ግን በምትኩ ለእርዳታ ወደ አሦር ህዝብ ይሄዳል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ኤፍሬም ለራሱ ፍቅረኞችን ቀጠረ

ኤፍሬም ከሌሎች ህዝቦች ጋር ያለው አንድነት የተገለጸው ኤፍሬም ለዘማዊነቱ እንደከፈላቸው ተደርጎ ነው፡፡ "የእስራኤል ህዝብ ለሌሎች አገራት ይጠብቋቸው ዘንድ ለመክፈል ሞከሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በሃያል ንጉሥ ተጽዕኖ ምክንያት

ይህም፣ የአሦር ንጉሥ፣ "ታላቁ ንጉሥ" ተብሎም ይጠራል፤ ህዝቡን ያስጨንቃልና ነው፡፡