am_tn/hos/08/06.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

ህዝቡ ነፋስን ይዘራል ዐውሎ ነፋስን ያጭዳል

ነፋስን መዝራት ወይም ነፋስን መትከል እርባና በሌለው ወይም አጥፊ በሆነ መንገድ መስራት ነው፡፡ ዐውሎ ነፋስን ማጨድ ከራስ ድርጊት የተነሳ በጥፋት መከራን መቀበል ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የቆመው ተክል ራስ/ዛላ የለውም

እዚህ ስፍራ "ራስ/ዛላ" የሚለው የሚያመለክተው ፍሬ የሚገኝበትን የተክሉን ክፍል ነው፡፡ ራስ/ዛላ የሌለው አገዳ ለገበሬም የሚሰው ምንም ነገር የለም፡፡ በተመሳሳይ መንገድ፣ የእስራኤ ድርጊቶች አንዳች መልካም ውጤት አያስገኝም፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ መድረስ ቢመጣም እንኳን፣ ባዕዳን ይበሉታል

ማናቸውም የእራኤል ድርጊት ጥሩ ውጤት ማምጣት ቢችል እንኳን፣ የእስራኤል ጠላቶች መጥተው ከእነርሱ ይወስዱታል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)