am_tn/hos/08/04.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው ነገር ግን የሆነው ይህ ነው፤ ተቆርጠው ሊወድቁ ይችላሉ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ነገር ግን ውጤቱ የሚሆነው እኔ ህዝቡን ማጥፋቴ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥጃችሁ ተቀባይነት አላገኘም

ሊሰጡ የሚችሉ አማራጭ ትርጓሜዎች 1) ይህ የነቢዩ ንግግር ነው፡፡ "ያህዌ የእናንትን ጥጃ አልተቀበለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ወይም 2) ያህዌ እየተናገረ ነው፡፡ "እኔ ራሴ የእናንተን ጥጃ አልተቀበልኩም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

የእናንተ ጥጃ

ህዝቡ ጥጃ የሚመስል ጣኦት ያመልካል፣ ስለዚህ ያህዌ ስለአምልኳቸው ራሱን ጥጃውን እንደሆነ አድርጎ እየተናገረ ነው፡፡ "ጥጃ ጣኦታችሁን ለምታመልኩ፣ የእናንተ አምልኮ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ቁጣዬ በእነዚህ ህዝቦች ላይ እየነደደ ነው

ቁጣ ብዙውን ጊዜ እንደ እሳት ተደርጎ ይነገራል፡፡ "እኔ በዚህ ህዝብ በጣም ተቆጥቻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እስከ መቼ በደለኛ ሆነው ይቀጥላሉ?

ያህዌ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ህዝቡ ንጹህ ባለመሆኑ ቁጣውን ለመግለጽ ነው፡፡ "በዚህ ህዝብ ላይ ተቆጥቻለሁ ምክንያቱም ንጹህ ለመሆን ምንም ፍላጎት የላቸውም፡፡" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)