am_tn/hos/07/12.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ

ይህ ወፎች የሚጠመዱበት መንገድ ነው፡፡ ያህዌ የእስራኤልን ህዝብ ከርግብ ጋር ማነጻጸሩን ቀጥሏል፡፡ እነርሱ ወደ ግብፅ ወይም አሦር ለእርዳታ ሲሄዱ፣ ያህዌ እነርሱን ይቀጣቸዋል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ሰማይ ወፎች እነርሱን ከላይ አወርዳቸዋለሁ

ያህዌ በእስራኤል ላይ የሚፈርድበትን መንገድ በመረብ የሚያጠምዳቸው ወፎች እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ "አዳኝ ወፎችን እንደሚያጠምድ እኔ እነርሱን አጠምዳቸዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አብረው ሲበሩ

ይህ አገላለጽ ወፎችን በማጥመድ የተገለጸውን ዘይቤያዊ አነጋገር አስፋፍቶ ያቀርባል፡፡