am_tn/hos/07/10.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

የእሰስራኤል ኩራት በራሱ ላይ ይመሰክርበታል

ይህ "ኩራትን" በፍርድ ቤት በእሰስራኤል ህዝብ ላይ እንደሚመሰክር አንድ ሰው አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ ይህ ማለት ኩራት የተሞላው ዝንባሌያቸው እና ባህሪያቸው ያህዌን መታዘዝ በማቆም በደለኛ እንዳደረጋቸው ያሳያል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወይም ደግሞ አላዩትም

የእስራኤል በያህዌ ላይ ፍላጎት ማጣት የተገለጸው ልክ እርሱ እንደጠፋ እና እነርሱም ሊፈልጉት ይሞክሩ እንዳልነበረ ነው፡፡ "ለእነርሱ ትኩረት እንዲሰጣቸው እነርሱም ሊያገኙት አይሞክሩም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ሁሉ ሆኖ

እዚህ ስፍራ "ይህ" የሚለው የሚያመለክተው እግዚአብሔር ባዕዳን እንዲያሸንፏቸው መፍቀዱን እና እነርሱን ደካማ እንዳደረጋቸው ነው፡፡

ኤፍሬም እንደ ርግብ ነው፣ ንቁ ያልሆነና የሚታለል

ርግብ ሞኝ ወፍ ናት ተብሎ ይታሰብ ነበር፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ግብፅ … አሦር

እነዚህ እስራኤል እርዳታ ልትጠይቃቸው የምትችላቸው ሃያላን መንግሥታት ነበሩ