am_tn/hos/07/06.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

የቤተ መንግሥት መኳንንት ሴራ ተገልጽዋል፡፡ ንጉሣቸውን ለመግደል የገፋፋቸው ቁጣቸው ነው፡፡

ልባቸው እንደ ጋለ ምድጃ ነው

ይህ ማለት በምድጃ ላይ እንደሚነድ እሳት፣ እነዚህ ሰዎች ጠንካራ ክፉ መሻቶች አሏቸው፡፡ የሰዎቹ መሻቶች በእነርሱ "ልቦች" ተገጽዋል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

ቁጣቸው ጤሰ

"ጤሰ" የሚለው ቃል ትርጉሙ አንድ ነገር ካለ ነበልባል ቀስ በቀስ ነደደ ማለት ነው፡፡ "ቁጣቸው በቀስታ እና በጸጥታ እያደገ ሄደ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ሚንበለበል እሳት ከፍ ብሎ ነደደ

የቁጣቸው ጥንካሬ የተገለጸው እግጅ የሚነድ እሳት እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ "በጣም እየከፋ ሄደ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘ፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው

ይህ የእነርሱን ቁጣ ከምድጃ እንደሚወጣ ሙቀት ያነጻጽረዋል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ገዢዎቻቸውን ፈጁ

ይህ የቤተ መንግሥት መኳንንት ነገስታቶቻቸውን ገደሉ ለማለት ይመስላል፡፡