am_tn/hos/07/03.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

ንጉሡን በክፋታቸው

የዕብራይስጡ ጽሁፍ በተለያዩ ስፍራዎች ግልጽ አይደለም፡፡ ሆኖም፣ ብዙዎች ይህንን የተረጎሙት የንጉሡ መኳንንት ለእግዚአብሔር ታማኝ እንዳልሆኑ በመግለጽ እና እንደዚሁም ንጉሡን ለመግደል እንዳቀዱ፣ ከዚያም በመቀጠል እቅዳቸውን እንደፈጸሙ ነው፡፡ ይህ ከአንድ ጊዜ በላይ የሆነ ይመስላል፡፡ እነዚህ ወንጀሎች የተገለጹት አገሪቱ እንደ ሰጠመችበት ክፋት መገለጫ ተደርገው ነው፡፡

እነርሱ ሁሉም ዘማዊያን ናቸው

ጣኦታትን በማምለክ እና ለያህዌ ታማኝ ባለመሆን መንፈሳዊ ዘማዊነት የፈጸሙ ሰዎች፡፡ እነዚህ ሰዎች ምናልባትም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመተኛት ለባሎቻቸው ወይም ለሚስቶቻቸው ታማኝ ያልነበሩ ናቸው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በዳቦ ጋጋሪው እንደጋለ ምድጃ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ ይህ ማለት ህዝቡ ክፉ ለማድረግ ጽኑ ፍላጎት አለው፡፡ "ዳቦ ጋጋሪ እንደሚቆሰቁሰው ምድጃ" (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የሊጡ መቡካት

ይህ ዳቦ የመድፋት ሂደት አንድ ክፍል ነው

በንጉሣችን የበዓል ቀን

ይህ ምናልባት በንጉሡ ተይዞ የሚከበር በዓል ይሆናል

እርሱ በገዛ እጆቹ አደረገ

ይህ ምናልባት ከአንድ ሰው ጋር መተባበር ወይን ማበር ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ንጉሡ ከመኳንንቱ ጋር ማፌዝ በሌለበት ነገሮች ወይም ሰዎች ምናልባትም በእግዚአብሔር እንኳ ሳይቀር አፌዘ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)