am_tn/hos/07/01.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እየተናገረ ነው

እስራኤልን መፈወስ እፈልጋለሁ

ዳግም እስራኤል ለእግዚአብሔር ታማኝ እንድትሆን ማድረግ እና የእርሱ በረከት ተቀባይነት የተገለጸው እንደ ፈውስ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ማታለንን ይለማመዳሉ

ሰዎች ምርቶችን የሚሸጡት እና የሚገዙት በሃሰት ነው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የዘራፊ ቡድን

ይህ ያለምክንያት ሌሎች ሰዎችን የሚያጠቃ ቡድን ነው

ድርጊታቸው ከቧቸዋል

እዚህ ስፍራ የሰዎቹ ክፉ ስራዎች የተነገሩት ምናልባት በወንጀላቸው ሊከሷቸው የተዘጋጁ ሌሎች ሰዎች እንደሆኑ ተደርገው ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ በፊቴ ናቸው

እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር የተገለጸው፣ መገኘቱን እና ህልውናውን በሚያጎላው በእርሱ "ፊት" ነው፡፡ "ደግሞም እኔ ሁሉንም አያለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ ዘይቤያዊ አነጋገር- የአንደን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)