am_tn/hos/06/04.md

1.5 KiB

አያያዥ ሃሳብ

ያህዌ እየተናገረ ነው

እናንተን ምን ላድርግ?

እግዚአብሔር ትዕግቱ እያለቀ መሆኑን እና የቀረው ፍርድ ብቻ እንደሆነ እየተናገረ ነው፡፡ " በእናንተ ላይ ምን እንደሚደረግ ማወቅ አስቸጋሪ ነው!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህም በነቢያቱ ቆራረጥኳቸው

ያህዌ በነቢያቱ አማካይነት፣ አመጸኛ በሆነው ህዝብ ላይ ጥፋትን አወጀ፡፡ እዚህ ስፍራ "ወደ ቁርጥራጭ መቆራረጥ" በሚል የተጠቀሰው ጥፋት እንደ ፍርዱ የተረጋገጠ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ድንጋጌዎችህ እንደ ብርሃናት ናቸው

እዚህ ስፍራ ነቢዩ ሆሴዕ ለእግዚአብሔር እየተናገረ ነው፡፡ እግዚአብሔር በአንድ ሰው ላይ የሞትን ትዕዛዝ ቅጣት አድርጎ ሲሰጥ እንደ አስደንጋጭ የሚመታ መብረቅ ይመስላል ማለቱ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይንም ልክ ብርሃን ነገሮች እንዲታዩ እንደሚያደርግ፣ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ሰዎች እውነቱን እንዲያውቁ ያደርጋቸዋል ማለቱ ሊሆን ይችላል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ድንጋጌዎችህ

"የያህዌ ትዕዛዛት"