am_tn/hos/06/01.md

1.7 KiB

አያያዥ ሃሳብ

የእስራኤል ህዝብ ለመመለስ ፍላጎታቸውን ተናገሩ

እርሱ ሰባብሮናል … እርሱ አቁስሎናል

እግዚአብሔር የእስራኤልን ህዝብ የቀጣው እርሱን ስላልታዘዙ እና ጣኦታትን ስለመለኩ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ይፈውሰናል… እርሱ ቁስላችንን ይጠግናል

እስራኤል እነርሱ ሲመለሱ እግዚአብሔር ምህረት እንደሚያበዛላቸው እና ከችግራቸው ነጻ እንደሚያወጣቸው ታምናለች፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከሁለት ቀናት በኋላ ያነቃናል፡ በሶስተኛው ቀን ያስነሳናል

ይህ የሚወክለው አጭር ጊዜን ነው፡፡ እስራኤል ከጠላቶቻቸው ሊያድናቸው እግዚአብሔር በቶሎ እንደሚመጣ ያምናሉ፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሁለት ቀናት … በሶስተኛው ቀን

"2 ቀናት … 3ተኛ ቀን" (ቁጥሮች እና ተከታታይ ቁጥሮች የሚሉትም ይመልከቱ)

ያህዌን እንወቅ

እዚህ ስፍራ "ማወቅ" ማለት የእግዚአብሔርን ባህሪ እና ህጎች ማወቅ ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ለስርሱ ታማኝ መሆንንም ይጨምራል፡፡

የእርሱ መምጣት እንደ ንጋት የተረጋገጠ ነው

ፀሐይ በየማለዳው መውጣቷ እርግጥ የሆነውን ያህል ያህዌ ህዝቡን ለመርዳት ይመጣል፡፡