am_tn/hos/05/12.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ስለ ይሁዳ እና እስራኤል እየተናገረ ነው፡፡

ለኤፍሬም እንደ ብል፣ ለይሁዳ ቤት እንደ ነቀዝ እሆናለሁ

ብል በቁራጭ ሱፍ ላይ ነቀዝ በቁራጭ እንጨት ላይ ሁለቱም አጥፊዎች ናቸው፡፡ ያህዌ ሁለቱንም መንግሥታት ያጠፋል (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ብል…ነቀዝ

እነዚህ ሁለት ቃላት በተለያየ መንገድ ይተረጎማሉ ምክንያቱም የዕብራይስጡ ቃል ትርጉም አንድም በጣም ሰፊ ነው ወይም በእርግጠኝነት ለመተረጎም ያዳግታል፡፡

ኤፍሬም ህመሙን፣ ይሁዳም ቁስሉን አየ

ኤፍሬም (የሰሜን እስራኤል መንግሥት) እና ይሁዳ (የደቡብ እስራኤል መንግሥት) ሁለቱም በአደጋ ውስጥ እንደሆኑ አውቀዋል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለሰውን ይመልከቱ)

ከዚያም ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፣ ይሁዳም ወደ ታላቁ ንጉሥ መልዕክተኛ ላከ

ኤፍሬም እና ይሁዳ ያህዌን እርዳታ ከመለመን ይልቅ አሦርን እርዳታ ለመኑ፡፡ "ታላቅ ንጉሥ" ለአሦር ነገሥታት ማዕረግ ነበር፡፡

እርሱ ግን አልቻለም

እዚህ ስፍራ "እርሱ" የሚለው የሚያመለክተው የአሦርን ንጉሥ ነው