am_tn/hos/05/10.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ስለ ይሁዳ እና እስራኤል እየተናገረ ነው፡፡

የይሁዳ መሪዎች የድንበር ምልክት የሆነ ድንጋይን እንደሚያነሱ ናቸው

"የድንበር ድንጋይ ማንሳት" የሚለው የሚያመለክተው የአንድ ሰው ድንበር የሆነን በመሬት ላይ የሚገኝ ምልክትን ማንቀሳቀስን ነው፤ ይህ በእስራኤል ህግ ወንጀል ነበር፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቁጣዬን በእነርሱ ላይ እንደ ውሃ አዘንባለሁ

በይሁዳ ላይ የያህዌ ቁጣ እንደሚያጠፋቸው ትልቅ ወራጅ ውሃ ይሆናል፡፡ በቅዱሳት መጽሐፍት፣ ስሜቶች እና የስነምግባር ደረጃዎች ብዙውን ጊዜ እንደ ፈሳሽ ሆነው ይገለጻሉ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ኤፍሬም የደቀቀ ነው፣ እርሱ በፍርድ የደቀቀ ነው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ ይህ ሃሳብ ትኩረት እንዲያገኝ ሁለት ጊዜ ተደጋግሞ ተጽፏል፡፡ እዚህ ስፍራ "ኤፍሬም" የሚለው የእስራኤልን ሰሜናዊ ግዛት ህዝብ ያመለክታል፡፡ "እኔ የእስራኤልን ህዝብ ክፉኛ እቀጣለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ፣ (ሲኔክቲኪ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ))

ጣኦታትን ተከትለዋል

እዚህ ስፍራ "ተከትለዋል" የሚለው የሚያመለክተው አምልኮን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጣኦታት

እዚህ ስፍራ "ጣኦታት" ተብሎ በተተረጎመው የዕብራይስጡ ቃል ትረጉሙ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፤ በዘመናዊ ትረጉሞች ውስጥ በተለያዩ ብዙ መንገዶች ተተርጉሟል፡፡