am_tn/hos/05/08.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ስለ እስራኤል እየተናገረ ነው በጊብዓ የቀንደ መለከትን ድምጽ፣ በራማ እንቢልታን ንፉ እዚህ ስፍራ "ቀንደ መለከት" እና "እንቢልታ" ማለት ተመሳሳይ ማለት ነገር ነው፡፡ ይህ ትዕዛዝ ለጊብዓ እና ራማ ሰዎች የተሰጠው ጠላት እየመጣ እንደሆነ ለማሳወቅ ነው፡፡ (ጥንድ ትረጉም/ደብሌት የሚለውን ይመልከቱ)

በቤትአዌን የለቅሶ ድምጽ አሰሙ፡ "ብንያም ሆይ፣ እኛ እንከተልሃለን!" በሉ

እዚህ ስፍራ "ብንያም" የሚለው የሚወክለው ከብንያም ወገን የሆኑ ወታደሮችን ነው፡፡ይህ ምናልባት ህዝቡን ወደ ጦርነት ለመምራት ለእነርሱ የቀረበ ጥያቄ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ዘመናዊ ትረጉሞች ይህንን አገላለጽ ለመተረጎም የተለያዩ ሙከራዎችን አድረገዋል፡፡ (ስኔክቲኪ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤትአዌን

ይህ ከተማ በእስራኤል ሰሜናዊ ግዛት እና በደቡባዊ ግዛት በቢንያም ነገድ ድንበር መሃል የሚገኝ ነበር፡፡ ይህንን በሆሴዕ 4፤15 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

በእስራኤል ነገዶች መሃል በእርግጥ የሚሆነውን አውጃለሁ/ተናግሬያለሁ

"እኔ ያወጅኩትን/የተናገርኩትን ለእስራኤል ነገዶች አደርገዋለሁ"