am_tn/hos/05/05.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ስለ እስራኤል እየተናገረ ነው

የእስራኤል ኩራት በራሱ ላይ ይመሰክርበታል

ይህ "ኩራትን" በእስራኤል ህዝብ ላይ በፍርድ ቤት በተቃውሞ እንደሚመሰክር አንድ ሰው አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ በኩራት የተሞላው ዝንባሌያቸው እና ባህሪያቸው ያህዌን መታዘዝን አሻፈረኝ በማለተቸው ጥፋተኞች መሆናቸውን ያሳያል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) ስለዚህ እስራኤል እና ኤፍሬም በጥፋታቸው ይሰናከላሉ፤ ይሁዳም ደግሞ አብሯቸው ይሰናከላል ከኩራታቸው እና ከበደላቸው የተነሳ ሁለቱ መንግሥታት ሙሉ ለሙሉ እግዚአብሔርን የማይታዘዙ ይሆናሉ፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለያህዌ ታማኞች አልነበሩም፣ ህጋዊ ያልሆኑ ልጆችን ወልደዋልና

አማራጭ ትረጉሞች ሊሆኑ የሚችሉት 1) ይህ ማለት እስራኤላዊያን ከሌሎች ህዝቦች ጋር ተጋብተው ነበር፤ ከእነርሱም ልጆች ወልደው ነበር ወይም 2) ይህ ማለት እስራኤላዊ ወላጆች ለያህዌ ታማኞች አልነበሩም ደግሞም ልጆቻቸው ጣኦታትን እንዲያመልኩ ያስተምሯቸው ነበር

የአዲስ ጨረቃ በዓላቸው፣ ከእርሻቸው ጋር እነርሱንም አብሮ ያጠፋቸዋል

የእስራኤል ህዝብ በአዲስ ጨረቃ በዓል ማክበር ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ በዚህ ስፍራ ይህ አገላለጽ የአዲስ ጨረቃ በዓል፣ ህዝቡን እና እርሻቸውን እንደሚበላ አውሬ የሚገልጸው ይመላል፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ይህንን አገላለጽ መተረጎም ከባድ ነው፣ ብዙ ትርጎሞች የሚተረጎሙት እንዲህ አይነቱን ስሜት ሳይረዱት ነው፡፡ ሆኖም፣ አጠቃላይ ትረጉሙ፤ ለእርሱ ታማኝ ባለመሆኑ እግዚአብሔር ህዝቡን ይቀጣዋል የሚል መሆኑ እርግጥ ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)