am_tn/hos/05/03.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ስለ እስራኤል እየተናገረ ነው

ኤፍሬምን አውቃለሁ፣ እስራኤልም ከእኔ የተሰወረ አይደለም

እዚህ ስፍራ "ኤፍሬም" እና "እስራኤል" ሁለቱም መላውን ሰሜን የእስራኤል መንግሥት እና በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታሉ፡፡ እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር እነርሱ ምን አይነት እንደሆኑ እና ምን እያደረጉ እንደሆነ ሁሉን አውቃለሁ ይላል፡፡ (ስኔክቲኪ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ፤ ሚቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠትእና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ኤፍሬም፣ አሁን አንተ እንደ አመንዝራ ሆነሃል

ኤፍሬም እንደ አመንዝራ ቀርቧል፣ ምክንያቱም አምንዝራ ሴት ለማንም ወንድ ታማኝ እንደማትሆን ህዝቡ ለእግዚአብሔር የማይታመን ሆኗል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዘማዊ አስተሳሰብ በውስጣቸው ስላል

ይህ ማለት ለእግዚአብሔር ታማኝ ያለመሆን ፍላጎት አላቸው፡፡ ጣኦታትን ማምለክ ይፈልጋሉ፡፡

ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ… ያህዌን አያውቁም

ተርጓሚው ይህንን "ወደ እኔ ለመመለስ… እኔን አያውቁም፣" ወይም "ወደ እኔ ለመመለስ… እኔን፣ ያህዌን አያውቁም " በሚል መተካት ይችላል፡፡

ያህዌን አያውቁም

ከእንግዲህ እስራኤል በማናቸውም መንገድ ያህዌን አይታዘዝም፡፡ አምላካቸው አድርገው ለያህዌ እውቅና አይሰጡም፡፡