am_tn/hos/05/01.md

1.7 KiB

አያያዥ ሃሳብ

ያህዌ ስለ እስራኤል እየተናገረ ነው

በምጽጳ መጥመድ፣ በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋል

ወጥመድ እና መረብ ሁለትም ነገሮች ታዳኝን ማጥጃ ናቸው፡፡ በዚህ ሁኔታ፣ ካህናቱ እና የንጉሥ ቤት ህዝቡን ወደ ጣኦት አምልኮ ሲያማልሉ ከያህዌ ሊያርቋቸው መንገዶችን አበጅተዋል፡፡ ምጽጳ እና ታቦር በእስራኤል ምድር ጣኦታት ማምለኪያ ስፍራዎች ነበሩ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

አመፀኞች ለግድያ በርትተዋል

እዚህ ስፍራ "አመፀኞች" የሚለው የሚያመለክተው ከያህዌ ርቆ የሸሸውን ህዝብ ነው፤ "ለግድያ በርትተዋል" የሚለው ንጹሃን ሰዎችን መግደልን ወይም ለአህዛብ ጣኦታት የሚቀርቡ እንስሳትን ማረድን ሊያመለክት ይችላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አመፀኞች

ተርጓሚው ይህንን "እናንተ አመፀኞች፣" ብሎ ሊተካው ይችላል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በትክክል ለአመፀኞች የእስራኤል ሰዎች እየተናገረ ነው፡፡

በማረድ

አንዳንድ ዘመናዊ ትርጉሞች የዕብራይስጡን አገላለጽ ክፋትን እንደሚገልጽ አድርገው ይተረጉሙታል

እኔ ሁሉንም እቀጣለሁ

ተርጓሚው ይህንን "እኔ ሁላችሁንም እቀጣለሁ" ብሎ ሊተካው ይችላል፡፡