am_tn/hos/04/17.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ስለ እስራኤል እየተናገረ ነው

ኤፍሬም ከጣኦት ጋር ተጣምሯል፤ እርሱን ተዉት

እዚህ ስፍራ "ኤፍሬም" መላውን ሰሜናዊ የእስራኤል ግዛት ይወክላል፡፡ ይህ አገላለጽ በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን የሚገልጽ ሚቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ያህዌን ከማምለክ ይልቅ ጣኦታትን ማምለክ መረጡ፡፡ ያህዌ ሆሴዕን ህዝቡን ከመንገዱ ይመለስ ዘንድ ለመገሰጽ እንዳይሞክር አዘዘው፡፡ የእስራኤል ህዝብ አይሰማም፡፡ (ስኔክቲኪ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ፤ እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚሉትን ዘይቤዎች ይመልከቱ)

መሪዎቿ ሀፍረታቸውን እጅግ ወደዱ

መሪዎቿ ጣኦታትን ሲያመልኩ እና በያህዌ ላይ ፊታቸውን ሲያዞሩ በሚያደርጉት አያፍሩም ነበር

ነፋስ በክንፎቹ ጠቅልሎ ይወስዳታል

እዚህ ስፍራ "ነፋስ" የሚለው የሚወክለው በእስራኤል መንግሥት ላይ የእግዚአብሔርን ፍርድ እና ቁጣ ነው፡፡ ያህዌ የጠላት ሰራዊት የእስራኤልን ህዝብ እንዲያሸንፍ እና ምርኮ አድርጎ እንዲውዳቸው ይፈቅዳል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ሚቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚሉትን ዘይቤያዊ አነጋገሮች ይመልከቱ)