am_tn/hos/04/11.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ስለ እስራኤል እየተናገረ ነው ሴሰኝነት፣ አሮጌ ወይን ጠጅ፣ እና አዲስ ወይን ጠጅ ማስተዋላቸውን ወስደውባቸዋል የእስራኤል ሰዎች ከጋብቻ ውጭ ይሴስናሉ፤ ደግሞም ብዙ የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ እነዚህን ነገሮች በማድረግ የያህዌን ትዕዛዛት ረሱ፡፡ እዚህ ስፍራ እነዚህ ድርጊቶች የተነገሩት ሌሎች ሰዎች ያህዌን የመታዘዛቸውን ጠቀሜታ እንዳይረዱ እንደሚከላከሉ ሰዎች ተደርገው ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዘንጎቻቸው ትንቢት ለመናገር ምሪት ሆናቸው

ጣኦት አምላኪዎች የወደፊቱን ለመተንበይ ዘንጎችን ይጠቀማሉ፡፡ እዚህ ስፍራ ዘንጎች የተነገሩት ትንቢትን እንደሚናገሩ ሰዎች ተደርገው ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሴሰኛ አስተሳሰብ አሳታቸው

ጣኦታትን ማምለክ እና ከቤተ ጣኦት አመንዝሮች ጋር መዘሞታቸው የእስራኤል ሰዎች በእነዚህ መንገዶች ሁሌም በያህዌ ላይ በደል እንዲፈጽሙ ፍላጎት አሳደረባቸው፡፡ እዚህ ስፍራ "አስተሳሰብ/አዕምሮ" የተነገረው ህዝቡ ያህዌን እንዳይታዘዝ ማሳመን እንደሚችል አንድ ሰው ተደርገው ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አሳቷቸው

ህዝቡ እንዲበድል አሳመኑ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)