am_tn/hos/04/06.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በምዕራፍ 4፡6 ያህዌ ስለ እስራኤል ህዝብ ለካህናቱ ይናገራል፡፡ በምዕራፍ 4፡7 ስለ ካህናቱ እርሱ ይናገራል እንጂ ለእነርሱ አይናገርም፡፡ ተርጓሚው የዩዲቢን ምሳሌነትን ሊከተል ይችላል፤ ይህም ያህዌን፣ ለካህናቱ ሲናገር በምዕራፍ 4፡7 እንደሚገልጸው አይነት ነው፡፡

ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ህዝቤ ጠፍቷል ምክንያቱም እናንተ፣ ካህናቱ፣ ይታዘዙኝ ዘንድ ስለ እኔ በሚገባ አላስተማራችኋቸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ዕውቀት

እዚህ ስፍራ "ዕውቀት" የሚለው የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን እውቀት ነው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ክብራቸውን በውርደት ለወጡ

አማራጭ ትረጉም ሊሆኑ የሚችሉት1) "ክብር" ያህዌን የሚወክል ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ሀፍረት" ጣኦታትን የሚወክል ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ " ታላቁን አምላካቸውን እኔን ማምለክ ትተዋለ፣ አሁን አሳፋሪ ጣኦታቶቻቸውን ያመልካሉ" 2) አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትረጉሞች ይህንን የሚተረጉሙት "ክብራቸውን በውርደት እለውጣለሁ" በሚል ነው፡፡ ይህ ማለት ያህዌ ካህናቱ የሚያከሯቸውን ነገሮች ይወስድባቸዋል ደግሞም ካህናቱ እንዲያፍሩ ያደርጋል፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)