am_tn/hos/04/01.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ ምዕራፍ ታማኝ ባልሆኑት እስራኤላዊያን ላይ የያህዌን ክርክር በማቅረብ ይጀምራል

ያህዌ ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ሙግት አለው

ያህዌ የእስራኤል ህዝብ እንደበደለው እና ቃል ኪዳኑን እንዳፈረሰ ይናገራል፤ ያህዌ ይህን የሚናገረው በፍርድ ቤት እንደሚከሳቸው አድርጎ ነው፡፡

ሙግት

ይህ በህግ አደባባይ አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ የሚያቀርበው ክርክር ነው፡፡ ይህንን በሆሴዕ 2፤2 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡

ህዝቡ ሁሉንም ወሰኖች ጥሰዋል

እዚህ ስፍራ "ወሰኖች" የሚለው የሚገልጸው ህጉ የሚፈቅደውን መጠን ነው፡፡ "ህዝቡ በሁሉም መንገድ ህጉን አልታዘዘም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)

በደም ማፍሰስ ላይ ደም ማፍሰስ ይጨምራል

እዚህ ስፍራ "ደም ማፍሰስ" የሚለው የሚገልጸው "ግድያን" ነው፤ ይህም ብዙውን ጊዜ የተጠቂውን ደም መፍሰስ ይጨምራል፡፡ "በግድያ ላይ ግድያ ጨመራችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት)