am_tn/hos/02/21.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ምን እንደሚያደርግ ለሆሴ እየተናገረ ነው፡፡

ይህ የያህዌ አዋጅ ነው/ ያህዌ የተናገረው ይህ ነው

ያህዌ የአዋጁን እርግጠኝነት ለመግለጽ ስለ እራሱ በስሙ ተናገረ፡፡ ይህንን በሆሴዕ 2፡13 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ያወጀው/የተናገረው ይህ ነው" ወይም "እኔ ያህዌ ያወጅኩት/የተናገርኩት ይህ ነው፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ምድር ለእህል፣ አዲስ ወይን፣ እና ለወይራ ዘይት ምላሽ ይሰጣል፤ እነርሱም ለኢይዝራኤል ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

ምድር ለእህል፣ አዲስ ወይን፣ እና ለወይራ ዘይት የሚያስፈልገውን ትሰጣለች፡፡ እነዚህ ነገሮች ደግሞ የኢዝራኤልን ፍላጎቶች ያሟላሉ፡፡ ምድሪቱ እና እነዚህ ምርቶች የሌሎችን ፍላጎት ማሟላት እንደሚችሉ ሰዎች ሆነው ተገልጸዋል፡፡ (ሰውኛ የሚለውን ዘይቤ ይመልከቱ)

ኢዝራኤል

እዚህ ስፍራ የዚህ ሸለቆ ሰም መላውን የእስራኤል ህዝብ ይወክላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)