am_tn/hos/02/19.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ምን እንደሚያደርግ ለሆሴ እየተናገረ ነው

ለዘለዓለም ባልሽ ልሆን ቃል ኪዳን እገባልሻለሁ

ያህዌ ልክ እንደ ባል ይሆናል፣ እስራኤል እንደ ያህዌ ሚስት ትሆናለች፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)

በጽድቅ፣ በፍትህ፣ ለቃልኪዳን ታማኝ በመሆን፣ እና በምህረት

ይህ ረቂቅ ስሞችን ለማስቀረት እንደገና ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ትክክል፣ፍትህ ያለበት፣ ታማኝ እና ምህረት የሞላበትን ነገር አድርጉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

አንቺም ያህዌን ታውቂያለሽ

እዚህ ስፍራ "ማወቅ" የሚለው እንደ አምላካቸው ለያህዌ እውቅና መስጠትንና ለእርሱ ታማኝ መሆንን ነው፡፡