am_tn/hos/02/16.md

1.7 KiB

በዚያን ቀን ይሆናል

ይህ የሚያመለክተው እስራኤል ያህዌን ብቻ ማምለክ የምትመርጥበትን ቀን ነው

ይህ የያህዌ አዋጅ ነው/ ያህዌ የተናገረው ይህ ነው

ያህዌ የአዋጁን እርግጠኝነት ለመግለጽ ስለ እራሱ በስሙ ተናገረ፡፡ ይህንን በሆሴዕ 2፡13 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ያወጀው/የተናገረው ይህ ነው" ወይም "እኔ ያህዌ ያወጅኩት/የተናገርኩት ይህ ነው፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ባሌ

ይህ ማለት ሚስት ለባሏ እንደምትሆን የእስራኤል ህዝብ ያህዌን የሚወድ እና ለእርሱ ታማኝ ይሆናል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)

በኣሌ

"በኣል" ማለት "ጌታ" ማለት ሲሆን ከነዓናውያን የሚያመልኳቸውን ሀሰተኛ አማልክትንም ያመለክታል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)

ከአንደበቷ የበኣልን ስሞች አስወደግዳለሁ

እስራኤላዊያን ዳግም የበኣልን ስሞች እና ጣዖታትን አይጠሩም፡፡ ህዝቡ የተወከለው በአንደበቶቻቸው ነው፡፡ "የበኣልን ስሞች እንዳትጠሩ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲኪ/ ዘይቤያዊ አነጋጋር- የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ፤ የሚለውን ይመልከቱ)