am_tn/hos/02/12.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ በእራኤል ላይ ስለሚያደርገው ለሆሴዕ እየተናገረ ነው

ፍቅረኞቼ ለእኔ የሰጡኝ ዋጋዎቼ/ክፍያዌቼ እነዚህ ናቸው

ይህ የሚያመለክተው እስራኤል ከሃሰተኛ አማልዕክት ወይም ከበኣል የተቀበለቻቸውን ክፍያዎች ነው፡፡ ይህ ቀጥተኛ ጥቅስ ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅስ ሆኖ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እንግዲህ እነዚህ ፍቅረኞቿ ለእርሷ የሰጧት ወጋዎች ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ ጥቅሶች የሚለውን ይመልከቱ)

ጫካ አደርገዋለሁ

ያህዌ ሌሎች ዛፎች እና አረም እንዲበቅል በመፍቀድ የወይን ተክሉን እና የፍሬ ዛፉን ያጠፋል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የያህዌ አዋጅ ነው/ ያህዌ የተናገረው ይህ ነው

ያህዌ የአዋጁን እርግጠኝነት ለመግለጽ ስለ እራሱ በስሙ ተናገረ፡፡ "ያህዌ ያወጀው/የተናገረው ይህ ነው" ወይም "እኔ ያህዌ ያወጅኩት/የተናገርኩት ይህ ነው፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)