am_tn/hos/02/04.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለሆሴዕ እየተናገረ ነው

የምንዝርና ልጆች ናቸውና

እስራኤላዊያን የሚያደርጉት የያህዌ ያልሆኑ ይመስል ነው፡፡ አባቶቻቸው እግዚአብሔርን እንዳላመለኩት ሁሉ፣ እነርሱም አላመለኩትም፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)

እናቶቻቸው አመንዝሮች እንደነበሩ

ሌሎች አማልዕክትን የተከተሉት የቀደሙት ትውልዶች ለያህዌ ታማኝ ባለመሆናቸው አመንዝሮች ተደርገው ነበር የተቆጠሩት፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)

ፍቅረኞቼን ተከትዬ እሄዳለሁ፣ እነርሱ ዳቦዬን እና ውሃዬን፣ የሃር ልብሴን እና ሱፌን፣ ዘይቴን እና መጠጤን ሰጥተውኛልና፡፡

እዚህ ስፈራ "ፍቅረኞቼ" የሚለው የሚያመለክተው እስራኤል ከያህዌ ይልቅ ልታመለክ የመረጠቻቸውን በዓልን እና ሌሎች ሃሰተኛ አማልዕክትን ነው፡፡ የተዘረዘሩት ነገሮች ሰዎች ለመኖር የሚያስፈልጓቸው ነገሮች ናቸው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)