am_tn/hos/02/02.md

2.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለሆሴዕ እየተናገረ ነው

ሙግት

ይህ በህግ አደባባይ አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ የሚያቀርበው ክርክር ነው

እናታችሁ

እዚህ ስፍራ "እናት" የሚለው የሚያመለክተው የእስራኤልን አገር ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሷ ሚስቴ አይደለችም

ያህዌ እስራኤልን እንደ ሴት እየተናገረ ለእርሱ ከእንግዲህ እንደ ሚስት እንዳልሆነች ይነግራታል፡፡ ይልቁንም እስራኤል ያህዌን ከመከተል እና ከማምለክ ፊቷን አዙራለች፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔም ባሏ አይደለሁም

ያህዌ ከእንግዲህ ከእስራኤል ጋር ባል ለሚስቱ እንደሚሆነው ግንኙነት ሊኖረው አይችልም፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)

የምንዝርና ተግባሯ

አመንዝራ የሆነች ሴት ከሌላ ሰው ጋር ለመተኛት ባሏን ትተዋለች፡፡ እስራኤል በያህዌ ላይ ያደረገችው እንደዚሁ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)

ከጡቶቿ መካከል

ይህ ምስላዊ ዘይቤ እስራኤል በያህዌ ላይ ሳይሆን በጣኦት መታመኗን ያሳያል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)

ዕርቃኗን ገፍፌ እንደተወለደችበት ቀን እራቁትነቷን እገልጣለሁ

ያህዌ ከእንግዲህ እስራኤልን አይጠብቃትም አይንከባከባትም፤ ምክንያቱም ከእርሱ እርቃለችና፡፡ በእስራኤል ባሎች ሚስቶቻቸውን ለማልበስ በህግ ይገደዱ ነበር፡፡ አንድ ወንድ ይህንን አለማድረጉ ሚስቱን ያለመቀበሉ ምልክት ነበር፡፡ የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ በረሃ አደርጋታለሁ

ያህዌ እስራኤልን ባዶ እና የማታበቅል በረሃማ ስፍራ እስክትመስል ይለውጣታል፡፡(ተነጻጻሪ ዘይቤ/ሲሚሊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከጥማት የተነሳ እገድላታለሁ

እዚህ ስፍራ "ጥማት" የሚለው የሚያመለክተው በጣኦታተት ላይ ሳይሆን፤ በያህዌ ላይ መታመንና እርሱን ማምለክ ያለውን አስፈላጊነት፣ ካልሆነ እስራኤል እንደ አገር መቀጠል የማትችል መሆኑን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)