am_tn/hag/02/10.md

1.3 KiB

በዘጠነኛው ወር በሃያ አራተኛው ቀን

ይህ በዕብራውያን ቀን አቆጣጠር ዘጠነኛው ወር ነው፡፡ በምዕራባውያን አቆጣጠር ሃያ አራተኛውን ቀን የሚውለው ታህሳስ አጋማሽ ላይ ነው፡፡

ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት

‹‹ዳርዮስ ንጉሥ በሆነ በሁለተኛው ዓመት›› ወይም፣ ‹‹ዳርዮስ ከነገሠ ሁለት ዓመት ሲሆነው››

ዳርዮስ… ሐጌ

የእነዚህን ሰዎች ስም እንዴት እንደ ተረጐምህ ሐጌ 1፥1 ተመልከት፡፡

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ጥቅም ላይ የዋለው ከእግዚአብሔር የመጣውን ልዩ መልእክት ለማመልከት ነው፡፡ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ሐጌ 1፥1 ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ መልእክት ሰጠ›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ይህን መልእክት ተናገረ››

ለያህዌ የተለየ ምግብ… ቅዱስ

‹‹ለያህዌ የተለየ›› እና ‹‹ቅዱስ›› የተሰኙት ቃሎች የአንድ የዕብራይስጥ ቃል ትርጉም ናቸው፡፡ ‹‹የተቀደሰ ምግብ… ቅዱስ››