am_tn/hag/02/01.md

1.2 KiB

በሰባተኛው ወር በሃያ አንደኛው ቀን

ይህ የዕብራውያን ቀን አቆጣጠር ሰባተኛ ወር ነው፡፡ በምዕራባውያን ቀን መቁጠሪያ ሃያ አንደኛው ቀን የሚውለው ጥቅምት አጋማሽ ላይ ነው፡፡

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ጥቅም ላይ የዋለው ከእግዚአብሔር የመጣውን ልዩ መልእክት ለማመልከት ነው፡፡ ሐጌ 1፥1 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፣ ‹‹ያህዌ መልእክት ሰጠ›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ይህን መልእክት ተናገረ››

በሐጌ እጅ

‹‹እጅ›› የሚለው ቃል ሐጌ ራሱን ያመለክታል፡፡ ይህን መልእክት ለመስጠት ያህዌ በሐጌ ተጠቅሞአል፡፡ 1፥1 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሐጌ በኩል››

ሐጌ… ዘሩባቤል… ሰላትያል… ኢያሱ… ኢዮሴዴቅ

የእነዚህ ሰዎች ስም እንዴት እንደ ተረጐምህ ሐጌ 1፥1 ተመልከት፡፡