am_tn/hag/01/14.md

1.5 KiB

ያህዌ የይሁዳን ገዥ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፣ የሊቀ ካህናቱን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስና ከምርኮ የተረፈውን ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አነሣሣ

መንፈስን ማነሣሣት ለሥራ ማነሣሣት ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የይሁዳን ገዥ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን እንዲሁም የሊቀ ካህናቱን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስና ከምርኮ የተረፈውን ሕዝብ ለሥራ አነሣሣ››

ትሩፋን

ባቢሎን ውስጥ በምርኮ የነበሩና በሕይወት ኖረው ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱ ሰዎች በስድስተኛው ወር ሃያ አራተኛው ቀን ይህ ማለት ራእዩ በመጣ በ23ኛው ቀን ማለት ነው፡፡ ይህ በአይሁድ አቆጣጠር ስድስተኛ ወር ነው፡፡ በምዕራውያን ቀን አቆጣጠር ሃያ አራተኛው ቀን የሚውለው መስከረም አጋማሽ ላይ ነው፡፡ በምዕራውያን ቀን አቆጣጠር ሃያ አራተኛው ቀን የሚውለው መስከረም አጋማሽ ላይ ነው፡፡

ዳርዩስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት

‹‹ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ ሁለተኛው ዓመት›› ወይም፣ ‹‹ዳርዮስ ንጉሥ በሆነ በሁለተኛው ዓመት››