am_tn/hag/01/03.md

1.7 KiB

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ከእግዚአብሔር የመጣ ልዩ ቃል ያመለክታል፡፡ ሐጌ 1፥1 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ መልእክት ሰጠ›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ይህን መልእክት ተናገረ››

በሐጌ እጅ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እጅ›› የሚለው ቃል የሚያመለክተው ራሱ ሐጌን ነው፡፡ ትእዛዙን ለሕዝቡ ለማድረስ ያህዌ በሐጌ በኩል ተጠቀመ፡፡ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ከሐጌ 1፥1 ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣

ይህ ጊዜው ነውን?

ያህዌ ሕዝቡን እየገሠጸ ነው፡፡ ይህ መልስ የማያስፈልገው ጥያቄ እንደ ዐረፍተ ነገር መተርጐም ይችላል፡፡ ‹‹ይህ ጊዜው አይደለም››

ይህ ቤት

የያህዌ ቤተ መቅደስ

መስከር አልቻላችሁም

መስከር ቀርቶ ጥምን ለማስታገሥ እንኳ በቂ ወይን ጠጅ የለም፡፡ ይህ ዐረፍተ ነገር መስከር ጥሩ ነገር ነው ማለት አለመሆኑን አንባቢው መረዳት አለበት፡፡

X

ደመወዝ ተቀበላችሁ ግን በቀዳዳ ኰረጆ የማስቀመጥ ያህል ነው የሆነባችሁ፡፡ አስፈላጊ ነገሮች ለመግዛት በቂ ገንዘብ አለማግኘት በቀዳዳ ኰረጆ ገንዘብ በማስቀመጥ ተመስሎአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሠራተኛው የተቀበለው ደመወዝ የሚያስፈልገውን ነገር ከመግዛቱ በፊት አለቀ››