am_tn/hag/01/01.md

1.6 KiB

ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት

‹‹በንጉሥ ዳርዮስ ሁለተኛ ዓመት›› ወይም፣ ‹‹ዳርዮስ ንጉሥ በሆነ በሁለተኛው ዓመት››

ዳርዮስ… ሐጌ… ዘሩባቤል… ሰላትያል.. ኢያሱ… ኢዮሴዴቅ

የሰዎቹ ስም በሙሉ እነዚህ ናቸው

በስድስተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን

‹‹በስድስተኛው ወር የመጀመሪያው ቀን፡፡›› ስድስተኛ ወር የሆነው በአይሁድ ቀን አቆጣጠር ነው፡፡ የመጀመሪያ ቀን በምዕራባውያን ቀን መቁጠሪያ ነሐሴ አጋማሽ ላይ ነው፡፡

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ ፈሊጣዊ ቃል ከእግዚአብሔር ስለ መጣ ልዩ ቃል ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፣ ‹‹ያህዌ መልእክት ሰጠ›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ ይህን መልእክት ተናገረ››

ያህዌ

ይህ ብሉይ ኪዳን ውስጥ ለሕዝቡ የተገለጠ የእግዚአብሔር ስም ነው፡፡ ይህ እንዴት እንደሚተረጐም ከቃላት ትርጉም ገጽ ስለ ያህዌ የተጻፈውን ተመልከት፡፡

በነቢዩ በሐጌ እጅ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እጅ›› የሚለው ቃል የሚያመለክተው ራሱ ሐጌን ነው፡፡ መልእክቱን ለማስተላለፍ ያህዌ በሐጌ በኩል ተጠቀመ፡፡ ሐጌ 1፥1 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፣ ‹‹በሐጌ በኩል››

የያህዌ ቤት

ቤተ መቅደሱ