am_tn/hab/01/15.md

2.3 KiB
Raw Permalink Blame History

X

1፥15-17 ላይ ያለው፣ ‹‹እርሱ›› እና፣ ‹‹የእርሱ›› የሚለው ነጠላ ቁጥር ሁሉንም የባቢሎን ወታደሮች የሚወክል አንድ የባቢሎን ወታደር ያመለክታል፡፡ ይህን ተውላጠ ስም ወደ ብዙ ቁጥር መለወጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያመጣናል… ሁላችንንም ይይዘናል››

በመረቡ ይይዛቸዋል፤ በአሽክላው ውስጥ ይሰበስባቸዋል

ይህ የሚናገረው ስለ አጠቃላይ ሰዎች ነው፡፡ ይህ ዕንባቆምንም እንዲጨምር አድርጐ ሊተረጐም ይችላል፡፡ ‹‹ሁላችንንም በመረቡ ይይዘናል፤ በአሽክላው ውስጥ ይሰበስበናል››

መንጠቆ… መረብ… አሽክላ

እነዚህ ዓሣ ለማጥመድ የሚጠቅሙ ናቸው፡፡

ለመረቡ ይሠዋል፤ ለአሽክላውም ያጥናል

ሕዝብንና መንግሥታትን ድል ለማድረግ ከለዳውያን የሚጠቀሙባቸው መሣሪያዎች ዓሣ ለማጥመድ የሚጠቀሙባቸው መሣሪያዎች ያህል መሆናቸውን ዕንባቆም ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎችን ድል ለማድረግ የሚጠቀሙባቸውን መሣሪያዎች መሥዋዕት ያቀርቡላቸዋል፤ ዕጣን ያጥኑላቸዋል››

ታዲያ መረቡን ባለ ማቋረጥ መጣል ሕዝቦችንስ ያለ ርኅራኄ መግደል አለበትን?

ዕንባቆም ይህን የሚጠይቀው ተስፋ ስለ ቆረጠና ይህ የሚቀጥለው ለምን ያህል ጊዜ መሆኑን ማወቅ ስለ ፈለገ ነው፡፡ ያህዌ ከለዳውያን ሕዝቦችንና መንግሥታትን ማጥፋታቸውን እንዲቀጥሉ ይፈቅድላቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መረባቸውን ባለ ማቋረጥ እንዲጥሉና ያለ አንዳች ርኅራኄ ሕዝቦችን እንዲያጠፉ ትፈቅድላቸዋለህን?

መረቡን ባለ ማቋረጥ መጣል

ያለ ማቋረጥ መረቡን እንደሚጥል ዓሣ አጥማጅ፣ ከለዳውያንም ተጨማሪ መንግሥታት ድል ለማድረግ እየተዘጋጁ መሆናቸውን ዕንባቆም ይናገራል፡፡