am_tn/hab/01/13.md

2.4 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ

ዕንባቆም ስለ ከለዳውያን ለያህዌ መናገሩን ቀጥሏል

ዐይኖችህ… እጅግ ንጹሐን ናቸው

እዚህ ላይ፣ ‹‹ዐይኖች›› ሁሉን የሚያይ ያህዌን ይወክላሉ፡፡ ‹‹አንተ እጅግ ንጹሕ ነህ››

ከሐዲዎችን

ይህ የሚያመለክተው ከለዳውያንን ነው፡፡ መካድ እምነተ ቢስና የተናገሩትን የሚያጥፉ፣ ሰዎችን ይመለከታል፡፡

ክፉው ከራሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠውስ ለምን ዝም ትላለህ?

ልክ የሚውጧቸው ይመስል፣ ክፉዎች ሌሎች ሰዎችን እንደሚያጠፉ ዕንባቆም ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ክፉ ሰው ከእርሱ የበለጠ ጻድቅ የሆነውን ሲያጠፋው ለምን ዝም ትላለህ?

ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን

ይህ የሚያመለክተው ዕንባቆም እየተናገረላቸው ያሉትን እስራኤላውያን ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ራሳቸው ክፉ መሆናቸውን፣ ሆኖም ከከለዳውያን፣ ‹‹ይልቅ ጻድቅ›› ወይም የከለዳውያንን ያህል ዐመፀኞች አለመሆናቸውን አንባቢው መረዳት አለበት፡፡

በባሕር ውስጥ እንዳለ ዓሣ አደረግሃቸው

ከለዳውያን ምንም ፀፀት ሳይሰማቸው ሌሎችን የሚገድሉበትን መንገድ፣ ዓሣ ሲያጠምዱ ምንም ፀፀት ከማይሰማቸው ሰዎች ጋር አመሳስሎአቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፣ ‹‹ሰዎች ከዓሣ የበለጠ ዋጋ እንዳይኖራቸው አደረግህ››

ገዥ እንደሌላቸውም የሚርመሰመሱ ፍጥረታት አደረግህ

‹‹የሚርመሰመሱ›› የሚለው ጥቃቅን ትሎችንና ፍጥረታት ያመለክታል፡፡ የሚርመሰመሱ ፍጥረታት የሚያደራጃቸውና የሚከላክልላቸው እንደሌላቸው ሁሉ፣ ሕዝቡ በከለዳውያን ሰራዊት ፊት መከላከያ የላቸውም፡፡ ግሡ ካለፈው ቁጥር ጋር የተያያዘ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል፡፡ ሰዎች ገዥ እንደሌላቸው የሚርመሰመሱ ፍጥረታት መከላከያ የሌላቸው እንዲሆኑ አደረግህ፡፡