am_tn/hab/01/12.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዕንባቆም ስለ ከለዳውያን ለያህዌ ይናገራል፡፡

ከዘላለም ጀምሮ ያለህ አይደለህምን? የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ

ዕንባቆም ይህን መልስ የማያስፈልገው ጥያቄ የሚያቀርበው አዎንታዊ ምላሽ በመጠበቅ ነው፡፡ እንደ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእርግጥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ ነህ፤ አምላኬ ያህዌ የእኔ ቅዱስ››

ከዘላለም ጀምሮ

‹‹ዘላለማዊ››

እንዲፈርዱ ሾመሃቸዋል፤ ዐለት ሆይ፣ ይቀጡ ዘንድ ሥልጣን ሰጠሃቸው፡፡

የሚናገረው ስለ ከለዳውያን ነው፡፡ ‹‹ፍርድ›› እና፣ ‹‹ቅጣት›› የተሰኙትን ቃሎች ግሥ አድርጐ መተርጐም ይቻላል፡፡ ከለዳውያን የያህዌ ሕዝብ ላይ እንደሚፈርዱና እንደሚቀጡ አንባቢው መረዳት አለበት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሕዝቡን እንዲቀጡ ሾምሃቸው፤ ዐለት ሆይ፣ ሕዝብህን እንዲቀጡ ሥልጣን ሰጠሃቸው››

ዐለት

ምንም ጉዳት እንዳይደርስበት ያህዌ ጠባቂው መሆኑንና ጠላቶቹ እንዳይደርሱበት የሚቆምት ዐለት መሆኑን ዕንባቆም ይናገራሉ