am_tn/hab/01/10.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ስለ ከለዳውያን ሰራዊት ገለጻውን ቀጥሏል፡፡

ነገሥታትን ይንቃሉ፤ በገዦችም ላይ ያፌዛሉ

በመሠረቱ የእነዚህ ሐረጐች ትርጒም ተመሳሳይ ነው፡፡ ‹‹ማፌዝ›› የሚለውን ቃል፣ ግሣዊ በሆነ ሐረግ መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ነገሥታትን ይንቃሉ፤ መሪዎችም ማላገጫዎቻቸው ናቸው፡፡›› ወይም፣ ‹‹እነርሱ የሚያደርጉት፣ ነገሥታትንና ገዦች ላይ ማፌዝ ብቻ ነው››

እንደ ነፋስ አልፈው ይሄዳሉ

በፍጥነት የሚንቀሳቀስ ነፋስ የሆኑ ይመስል፣ የከለዳውያን ሰራዊት እያንዳንዱን ድል በማድረግ ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው እንደሚሸጋገሩ ያህዌ ይናገራል፡፡

ጉልበታቸውን አምላካቸው ያደረጉ በደለኞች ናቸው

ይህ የሚያመለክተው የከለዳውያንን ሠራዊት ነው፡፡