am_tn/hab/01/08.md

1.6 KiB

ፈረሶቻቸው… ፈረሶቻቸው

የከለዳውያን ሰራዊት ፈረሶች

ነብር

ግዙፍ፣ ፈጠን ድመት

የማታ ተኩላ

ምግባቸውን ማታ ማታ የሚያድኑ ተኩላዎች ያመለክታል፡፡

ፈረሰኞቻቸው

ፈረሶች የሚጋልቡ የከለዳውያን ሰራዊት

ነጥቆ ለመብላት እንደሚቸኩል አሞራ ይበራሉ

አሞራ ምግቡን ለመያዝ ፈጣን እንደ ሆነ ሁሉ፣ ከለዳውያንም ጠላቶቻቸውን ድል ለማድረግ ምን ያህል ፈጣን መሆናቸውን ያህዌ ይናገራል፡፡

ሰራዊታቸው እንደ ምድረ በዳ ነፋስ ወደ ፊት ይገሠግሣል

ምድረ በዳ ላይ እንደሚነፍስ ነፋስ ከለዳውያን ምን ያህል በፍጥነት እንደሚንቀሳቀሱ ያህዌ ይናገራል፡፡

ምርኮኞችን እንደ አሸዋ ይሰበስባል

ይህን፣ 1) አንድ ሰው በእጁ አሸዋ እንደሚያፍስ ከለዳውያንም በቀላሉ ሰዎችን ምርኮኛ እንደሚያደርጉ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንድ ሰው አሸዋ እንደሚሰበስብ እነርሱም ምርኮኛ ይሰበስባሉ›› ወይም 2) እነዚያ ሰዎች ምድረ በዳ ውስጥ እንዳለ አሸዋ የሆኑ ይመስል፣ ከለዳውያንም እጅግ ብዙ ምርኮኛ ይሰበስባሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የምድረ በዳ አሸዋ የሚያህል ምርኮኛ ይሰበስባሉ››