am_tn/hab/01/03.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዕንባቆም ወደ እግዚአብሔር መጮኹን ቀጥሏል፡፡

ጥፋትና ግፍ በፊቴ አለ

‹‹ጥፋት›› እና ‹‹ግፍ›› የተሰኙትን ቃሎች ግሣዊ ሐረግ አድርጐ መተርጐም ይቻላል፡፡ ‹‹በፊቴ›› የሚለው ፈሊጥ እነዚህ ነገሮች የተፈጸሙት ዕንባቆም በዐይኑ እየተመለከተ እንደ ነበር ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች ነገሮችን ሲያጠፉና ግፍ ሲፈጽሙ በዐይኔ ዐይቻለሁ›› ጠብና ጭቅጭቅ በዝቶአል ‹‹ጠብ›› የሚለው ቃል በሰዎች መካከል አለ መግባባት መኖሩን የሚያመለክት ሲሆን፣ እንደ ግሣዊ ሐረግ መተርጐም ይቻላል፡፡ ልክ አንድ ሰው ወደ ላይ ከፍ ያለ ይመስል ዕንባቆም በሰዎችም መካከል ጠብ ከፍ እያለ መምጣቱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሰዎች መካከል ጠብ እየበዛ መጥቷል››

ክፉዎች ጻድቃንን ይከባሉ

ክፉዎች ጻድቃንን የመክበበቸውን ያህል ዐመፀኞች ጻድቃን ላይ ብዙ ግፍና መከራ እየፈፀሙ እንደ ሆነ ዕንባቆም ይናገራል፡፡

ሕግ ደክሟል

ሰዎች ለሕጉ አለ መታዘዛቸውን ወይም ተግባር ላይ አለማዋላቸውን ዕንባቆም የሕግ መድከምንና ምንም ማድረግ አለመቻልን ደካማ ከመሆን ጋር አመሳስሎታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማንም ሕግ አያከብርም››

ሐሰተኛ ፍርድ በዝቶአል

ዳኞች ትክክል የሆነ ፍርድ እንዳደረጉ ቢናገሩም፣ ለሕዝቡ ግን ‹‹ሐሰተኛ ፍርድ›› ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዳኞች በሐሰት ይፈርዳሉ››