am_tn/hab/01/01.md

1.3 KiB
Raw Permalink Blame History

ነቢዩ ዕንባቆም የተቀበለው መልእክት

እነዚህ ቃሎች የመጽሐፉን ሁለት ምዕራፎች ያስተዋውቃሉ፡፡ ዕንባቆም ይህን መልእክት ከያህዌ መቀበሉ ይታወቃል፡፡ ይህን የተሟላ ዐረፍተ ነገር አድርጐ ማቅረብ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፣ ‹‹ነቢዩ ዕንባቆም ከያህዌ የተቀበለው መልእክት ይህ ነው፡፡››

ያህዌ

ይህ በብሉይ ኪዳን ለሕዝቡ የተገለጠ የእግዚአብሔር ስም ነው፡፡ ይህን እንዴት እንደምትተረጉመው ከቃላት ትርጒም ስለ ያህዌ የተነገረውን ተመልከት፡፡

ለርዳታ እየተጣራሁ አንተ የማትሰማው እስከ መቼ ነው?

ያህዌ እንዲረዳው ዕንባቆም ረጅም ጊዜ ወደ እርሱ ሲጮኽ እንደ ነበር አንባቢ መረዳት አለበት፡፡ ተስፋ በመቁረጡና ያህዌ እስኪመልስለት ድረስ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለበት ማወቅ ስለ ፈለገ ይህን ጠይቆአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ መልስ እስክትሰጠኝ ከእንግዲህ ለርዳታ መጮኽ ያለብኝ ምን ያህል ጊዜ ነው?